am_tw/bible/kt/promisedland.md

2.4 KiB

የተስፋ ምድር

“የተስፋ ምድር” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች እንጂ በጠቅላላው መጽሐፍ ቅዱስ አይደለም። ለአብርሃምና ለዘሮቹ እንደሚሰጥ እግዚአብሔር ቃል የገባላት የምድረ ከነዓን አማራጭ ቃል ነው።

  • አብራም በዑር ከተማ በነበረ ጊዜ እንዲሄድና በከነዓን ምድር እንዲኖር እግዚአብሔር አዘዘው። እርሱና የእርሱ ዘሮች የሆኑት እስርኤላውያን ለብዙ ዓመታት እዚያ ኖሩ።
  • እዚያ ከደረሰው ድርቅ የተነሣ ራብ በሆነ ጊዜ እስራኤላውያን ወደ ግብፅ ሄዱ።
  • ክአራት መቶ ዓመት በዓላ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት አውጥቶ እንደሚሰጣቸው እግዚአብሔር ወደ ገባላቸው ምድር ወደ ምድረ ከነዓን አመጣቸው።

ነቢይ፣ ትንቢት፣ ትንቢት ተናገረ፣ ተመልካች፣ ነቢዪት “ነቢይ” የእግዚአብሔርን መልእክት ለሰዎች የሚናገር ሰው ነው። ይህን የምታደርግ ሴት ነቢዪት ትባላለች።

  • ነቢይ የሚለው የቀድሞ መጠሪያ፣ “ተመልካች” ሲሆን፣ “የሚያይ፣ የሚመለከት ሰው” ማለት ነው።
  • ይሁን እንጂ “ተመልካች” የሚለው ቃል አንዳንዴ ሟርተኛን ወይም ሐሰተኛ ነቢይንም ያመለክታል።
  • ምንጊዜም ነቢያት ሰዎች በኀጢአታቸው እንዲመለሱና ለእግዚአብሔር እንዲታዘዙ ያስጠነቅቃሉ።
  • “ትንቢት” ነቢዩ የሚናገረው መልእክት ነው። “ትንቢት መናገር” የእግዚአብሔርን መልእክት መናገር ማለት ነው።
  • ብዙውን ጊዜ የትንቢት መልእክት ወደ ፊት የሚሆነውን ያመለክታል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያሉ ብዙ ትንቢቶች ተፈጽመዋል።
  • “ሐሰተኛ ነቢይ” በአልን ከመሳሰሉ ሐሰተኛ አማልክት ተቀብያለሁ የሚለውን መልእክት የሚናገር ወይም የእግዚአብሔር መልእክት እንደ ተቀበለ በውሸት የሚናገር ሰው ነው።