am_tw/bible/other/vision.md

7 lines
848 B
Markdown

# ራእይ
“ራእይ” የሚለው ቃል አንድ ሰው የሚያየውን ያመለክታል። በተለይ ደግሞ የሚያመለክተው መልእክት ለመስጠት ባልተለመደ ወይም ልዕለ ተፈጥሮአዊ መንገድ እግዚአብሔር ለሰዎች የሚያሳየውን ያመለክታል።
* ብዙውን ጊዜ ራእይ የሚታየው ሳይተኙ ወይም ሳያንቀላፉ ነው። አንዳንዴ ግን ሰውየው ተኝቶ እያለ የሚያየው ሕልምም ራእይ ይባላል።
* እግዚአብሔር ለሰዎች ራእይ የሚያሳየው በጣም አስፈላጊ ነገር ሊነግራቸው ነው። ለምሳሌ ጴጥሮስ አሕዛብን በሙሉ ልቡ መቀበል እንዳለበት ለመናገር እግዚአብሔር ራእይ አሳይቶት ነበር።