# ራእይ “ራእይ” የሚለው ቃል አንድ ሰው የሚያየውን ያመለክታል። በተለይ ደግሞ የሚያመለክተው መልእክት ለመስጠት ባልተለመደ ወይም ልዕለ ተፈጥሮአዊ መንገድ እግዚአብሔር ለሰዎች የሚያሳየውን ያመለክታል። * ብዙውን ጊዜ ራእይ የሚታየው ሳይተኙ ወይም ሳያንቀላፉ ነው። አንዳንዴ ግን ሰውየው ተኝቶ እያለ የሚያየው ሕልምም ራእይ ይባላል። * እግዚአብሔር ለሰዎች ራእይ የሚያሳየው በጣም አስፈላጊ ነገር ሊነግራቸው ነው። ለምሳሌ ጴጥሮስ አሕዛብን በሙሉ ልቡ መቀበል እንዳለበት ለመናገር እግዚአብሔር ራእይ አሳይቶት ነበር።