am_tw/bible/other/trumpet.md

8 lines
732 B
Markdown

# መለከት
“መለከት” ሙዚቃ ለመጫወት ወይም ዐዋጅ ለማሰማት ወይም ሕዝብን ለስብሰባ ለመጥራት ጥቅም ላይ የሚውል መሣሪያ ነው።
* ብዙውን ጊዜ መለከት የሚሠራው ከብረት፣ ከባሕር እንስሳ ቅርፊት ወይም ከከብት ቀንድ ነበር።
* ሰዎች ለጦርነት እንዲሰበሰቡና በእስራኤል ሕዝባዊ ስብሰባ ጊዜ መለከት መነፋቱ የተለመደ ነበር።
* በመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ላይ እንደሚወርድ ለማስታወቅ መላእክት መለከት እንደሚነፉ የዮሐንስ ራእይ ይናገራል።