# መለከት “መለከት” ሙዚቃ ለመጫወት ወይም ዐዋጅ ለማሰማት ወይም ሕዝብን ለስብሰባ ለመጥራት ጥቅም ላይ የሚውል መሣሪያ ነው። * ብዙውን ጊዜ መለከት የሚሠራው ከብረት፣ ከባሕር እንስሳ ቅርፊት ወይም ከከብት ቀንድ ነበር። * ሰዎች ለጦርነት እንዲሰበሰቡና በእስራኤል ሕዝባዊ ስብሰባ ጊዜ መለከት መነፋቱ የተለመደ ነበር። * በመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር ቁጣ ምድር ላይ እንደሚወርድ ለማስታወቅ መላእክት መለከት እንደሚነፉ የዮሐንስ ራእይ ይናገራል።