am_tw/bible/other/tradition.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown

# ባሕል
ባሕል የሚያመለክተው ለረጅም ዘመን የተያዘና ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ ወግ ወይም ልማድ ነው።
* እስራኤላውያን ይዘዋቸው የነበሩ ብዙ ባሕሎች በጊዜ ሂደት በኋላ የሃይማኖት መሪዎቹ የጨምሩት እንጂ በብሉይ ኪዳን የታዘዙ አልነበሩም።
* አንዳንድ ጥቅሶች “የሰዎችን ባሕሎች” ይዘዋል፤ ይህም አይሁድ ይለማመዷቸው የነበሩ በኋላ የተጨመሩ እንጂ፣ የእግዚአብሔር ትእዛዞች እንዳልሆኑ ግልጽ ያደርጋል።
* አንዳንድ፣ “ባሕሎች”እግዚአብሔር የሰጠው ትእዛዞችንና እንዲሁም የሰዎች ሃይማኖታዊ ባሕልን ያካተቱ በመሆናቸው አጠቃላይ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላሉ።
* በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያኖች የሚለማመዷቸው ብዙ ባሕሎች የቅዱሳት መጻሕፍት ድጋፍ የላቸውም፤ ይሁን እንጂ፣ በታሪክ ውስጥ ተቀባይነት እያገኙ የመጡ ልማድና አሠራሮች ናቸው።