am_tw/bible/other/stronghold.md

1.2 KiB
Raw Permalink Blame History

ምሽግ፣ መከላከያ፣ የተመሸገ

“ምሽግ” ወይም፣ “መከላከያ” የጠላት ወታደሮችን ጥቃት መከለከል እንዲቻል በሚገባ የታጠረ ወይም ከለላ ያለው ቦት ማለት ነው። “የተመሸገ” ከተባለ አንድን ከተማ ወይም ምሽግ ለመከላከል በጠንካራ ግንቦች ዐለቶችና ሌሎች ጠንካራ ነገሮች ማጠርን ያመለክታል

  • ጠንካራ ሕንፃዎች፣ መከላከያ አጥሮች ወይም ዐለታማ ገደሎችን የመሳሰሉ የተፈጥሮ መከላከያዎች ወይም ትልልቅ ተራሮች ምሽግ ወይም መከለከያ ሊሆኑ ይችላሉ
  • በምሳሌያዊ መልኩ፣ “ምሽግ” ሐሰተኛ አማልክትን የመሳሰሉ አንድ ሰው በስሕተት የሚታመንባቸው ነገሮች ማለት ነው
  • “የተመሸገ” የሚለው፣ “በሚገባ የተከለለ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል
  • “ምሽግ” ወይም፣ “መከላከያ” “ጥበቃ የሚደረግለት ቦታ” ወይም፣ “ጠንካራ መከላከያ ያለው ቦታ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል