am_tw/bible/other/storehouse.md

10 lines
1.3 KiB
Markdown

# ጎተራ
“ጎተራ” ምግብ ወይም ሌሎች ነገሮችን ለማከማቸት የሚያገለግል ማስቀመጫ ነው
* መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበት አመን አብዛኛውን ጊዜ፣ “ጎተራ” ጥቅም ላይ የሚውለው ከረሃብ የተነሣ የምግብ እጥረት ሲኖር ለመጠቀም ትርፍ እህልንና ሌሎች ምግቦችን ለማከማቸት ነበር
* አንዳንድ ጊዜ የቤተሰቡን ሀብት ለማጠራቅም ጎተራ ጥቅም ላይ ይውላል
* ይህ ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ መስጠት የሚፈልገውን መልካም ነገር ሁሉ ያመልክታል
* ከተሸነፉ ጠላቶች የተወሰዱና ለያህዌ የተቀደሱ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ሁሉ የሚጠበቁት ያህዌ ቤት ውስጥ ባለው ጎተራ ነበር። ይህ ሀብት ቤተመቅደስን ማደሻ እንዲሆን ይከማቻል። አንዳንዴም፣ “ግምጃ ቤት” ይባላል
* “ጎተራ” የሚለውን ቃል ለመተርጎም ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ቃሎች፣ “እህል ማጠራቀሚያ” ወይም፣ “ምግብ ማከማቻ” ወይም፣ “ዋጋ ያላቸው ነገሮች የሚቀመጡበት” የተሰኙት ናቸው