am_tw/bible/other/sorcery.md

9 lines
1.3 KiB
Markdown

# ሟርት፣ ጥንቆላ
“ሟርት” ወይም “ጥንቆላ” አስማት በመጠቀም በክፉ መናፍስት ርዳታ አስደናቂ ነገሮችን ማድረግን ያመለክታል። በእነዚህ አስማታዊ ኅይሎች አስደናቂ ነገሮች የሚያደርገው ሰው ሟርተኛ ይባላል
* ሰዎች አስማታዊ ኅይልና ሟርት በመጠቀም በሽተኛን መፈወስ፣ ሌላው ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረግ ይችላሉ። ያም ሆኖ ግን፣ በክፉ መናፍስት ኅይል ስለሚጠቀም ማንኛውም የጥንቆላ ወይም የሟርት ዓይነት የተከለከለ ነው
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥንቆላና ሟርት እንደ ዝሙት፥ ጣዖት ማምለክና ስርቆት ሁሉ ኅጢአት መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሯል
* “ጥንቆላ” እና፣ “ሟርት” የሚለውን፣ “የክፉ መናፍስት ኅይል” ወይም፣ “ሰይጣናዊ አሠራር” ፣ “የአስማት ሥራ” በማለት መተርጎም ይቻላል
* “ሟርተኛ” የሚለው ቃል፣ “አስማት የሚሠራ” ወይም፣ “ደጋሚ” ወይም፣ “በክፉ መናፍስት ኅይል ተአምር የሚሠራ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል