# ሟርት፣ ጥንቆላ “ሟርት” ወይም “ጥንቆላ” አስማት በመጠቀም በክፉ መናፍስት ርዳታ አስደናቂ ነገሮችን ማድረግን ያመለክታል። በእነዚህ አስማታዊ ኅይሎች አስደናቂ ነገሮች የሚያደርገው ሰው ሟርተኛ ይባላል * ሰዎች አስማታዊ ኅይልና ሟርት በመጠቀም በሽተኛን መፈወስ፣ ሌላው ላይ ጉዳት እንዲደርስ ማድረግ ይችላሉ። ያም ሆኖ ግን፣ በክፉ መናፍስት ኅይል ስለሚጠቀም ማንኛውም የጥንቆላ ወይም የሟርት ዓይነት የተከለከለ ነው * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥንቆላና ሟርት እንደ ዝሙት፥ ጣዖት ማምለክና ስርቆት ሁሉ ኅጢአት መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሯል * “ጥንቆላ” እና፣ “ሟርት” የሚለውን፣ “የክፉ መናፍስት ኅይል” ወይም፣ “ሰይጣናዊ አሠራር” ፣ “የአስማት ሥራ” በማለት መተርጎም ይቻላል * “ሟርተኛ” የሚለው ቃል፣ “አስማት የሚሠራ” ወይም፣ “ደጋሚ” ወይም፣ “በክፉ መናፍስት ኅይል ተአምር የሚሠራ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል