1.1 KiB
1.1 KiB
ጥላ
ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ጥላ” ብርሃን ሲጋረድ የሚፈጠረውን ጨለማ ያመለክታል። በርካታ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት
- “የሞት ጥላ” ማለት ጥላ ለአንድ ነገር ቅርብ የሆነውን ያህል በዙሪያው ሞት አለ፤ ሞት ቅርብ ነው፤ አጠገብ ነው ማለት ነው
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰው ሕይወት ብዙ ከማይቆይና እውን ካልሆነ ጥላ ጋር ብዙ ጊዜ ተመሳስሏል
- አንዳንዴ፣ “ጥላ” – “ጨለማ” ለማለት ሌላ ቃል ነው
- መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ክንፎች ወይም እጆች ጥላ ውስጥ ስለመሸሸግ ይናገራል። ይህም ከአደጋ መከለልንና መደበቅን ያመለክታል። እንዲህ ባለው ዐውድ ውስጥ፣ “ጥላ” የሚለውን፣ “ከለላ” ወይም፣ “መደበቂያ ቦታ” በማለት መተርጎም ይቻላል
- “ጥላ” የሚለውን የአካባቢው ቋንቋ በሚጠቀምበት ሁኔታ ቃል በቃል መተርጎሙ ይመረጣል