am_tw/bible/other/shadow.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጥላ
ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ጥላ” ብርሃን ሲጋረድ የሚፈጠረውን ጨለማ ያመለክታል። በርካታ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት
* “የሞት ጥላ” ማለት ጥላ ለአንድ ነገር ቅርብ የሆነውን ያህል በዙሪያው ሞት አለ፤ ሞት ቅርብ ነው፤ አጠገብ ነው ማለት ነው
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰው ሕይወት ብዙ ከማይቆይና እውን ካልሆነ ጥላ ጋር ብዙ ጊዜ ተመሳስሏል
* አንዳንዴ፣ “ጥላ” “ጨለማ” ለማለት ሌላ ቃል ነው
* መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ክንፎች ወይም እጆች ጥላ ውስጥ ስለመሸሸግ ይናገራል። ይህም ከአደጋ መከለልንና መደበቅን ያመለክታል። እንዲህ ባለው ዐውድ ውስጥ፣ “ጥላ” የሚለውን፣ “ከለላ” ወይም፣ “መደበቂያ ቦታ” በማለት መተርጎም ይቻላል
* “ጥላ” የሚለውን የአካባቢው ቋንቋ በሚጠቀምበት ሁኔታ ቃል በቃል መተርጎሙ ይመረጣል