am_tw/bible/other/sex.md

9 lines
1.3 KiB
Markdown

# የግብረ ሥጋ ኅጢአት
“የግብረ ሥጋ ኅጢአት” የሚባለው በወንድና በሴት መካከል ካለው ጋብቻ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ነው። እንዲህ ያለው ከእግዚአብሔር ዕቅድ ውጪ ነው።
* ይህ ቃል ግብረ ሰዶማዊነትንና ወሲብ ነክ ስዕሎችን ጨምሮ ከእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጋጭ ማንኛውንም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያመለክታል። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች፣ “ሴሰኝነት” ይሉታል
* አንዱ የግብረ ሥጋ ኅጢአት ዝሙት ሲሆን፣ ይህ የሚያመለክተው ከባልና ከሚስት ግንኙነትና የትዳር ጓደኛ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ነው
* ሌላው የግብረ ሥጋ ኅጢአት፣ “ዝሙት አዳሪነት” ሲሆ፣ አስከፍለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ ሰውን ይመለከታል
* ይህ ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ሐሰተኛ አማልክትን በማምለክ እስራኤል ለእግዚአብሔር ታማኝ እንዳልነበሩ ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል