# የግብረ ሥጋ ኅጢአት “የግብረ ሥጋ ኅጢአት” የሚባለው በወንድና በሴት መካከል ካለው ጋብቻ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ነው። እንዲህ ያለው ከእግዚአብሔር ዕቅድ ውጪ ነው። * ይህ ቃል ግብረ ሰዶማዊነትንና ወሲብ ነክ ስዕሎችን ጨምሮ ከእግዚአብሔር ፈቃድ የሚጋጭ ማንኛውንም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ያመለክታል። አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች፣ “ሴሰኝነት” ይሉታል * አንዱ የግብረ ሥጋ ኅጢአት ዝሙት ሲሆን፣ ይህ የሚያመለክተው ከባልና ከሚስት ግንኙነትና የትዳር ጓደኛ ውጪ የሚደረግ ማንኛውም የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ነው * ሌላው የግብረ ሥጋ ኅጢአት፣ “ዝሙት አዳሪነት” ሲሆ፣ አስከፍለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ ሰውን ይመለከታል * ይህ ቃል ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ሐሰተኛ አማልክትን በማምለክ እስራኤል ለእግዚአብሔር ታማኝ እንዳልነበሩ ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል