am_tw/bible/other/send.md

9 lines
1.5 KiB
Markdown

# ላከ፣ መላክ
“ላከ” አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄድ ማድረግ ማለት ነው። አንድን ሰው፣ “መላክ” አንድን ነገር እንዲያደርግ ወይም አንድን ተልዕኮ እንዲፈጽም መናገር ወይም ማዘዝ ማለት ነው
* ሰዎች የሚላኩበት ራሱን የቻለ ዓላማ ይኖራል። ብዙ ጊዜ የሚላከው ሰው የተላከበትን ጉዳይ የመፈጸምና የማስፈጸም ኅላፊነትም ይሰጠዋል
* “ዝናብ ላከ” ወይም፣ “መዐት ላከ” የተሰኙት ሐረጎች፣ “እንዲመጡ ማድረግ” የሚል ትርጉም አላቸው። ይህ ዐይነቱ አነጋገር ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔር እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ በሚያደርግበት ጊዜ ነው
* “ቃል ላከ” ወይም፣ “መልእክት ላከ” በተሰኙት አነጋገሮች ውስጥ፣ “ላከ” ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ፣ ለሌሎች የምንናገረው ቃል ወይም መልእክት ሰጠን የሚል ትርጉም ይኖረዋል
* ለአንድ ሰው አንድ ዓይነት እንስሳ ወይም አንድ ነገር መላክ፣ እነዚያን ነገሮች ለሰውየው መስጠት ማለት ነው፤ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ነገሮች ለተቀባዩ ለማድረስ ጥቂት ጉዞ ማድረግ ያስፈልግ ይሆናል