1.2 KiB
1.2 KiB
መጠጊያ፥ መጠለያ
“መጠጊያ” የሚለው ቃል ዋስትናና ጥበቃ ያለበትን ቦታን ወይም ሁኔታን ያመለክታል። “መጠለያ” ከዝናብ ወይም ከአደጋ የሚከልል ነገር ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሕዝቡ ጥበቃ፣ ጥንቃቄና ሰላም የሚያገኙበት መጠጊያ እንደ ሆነ ተነግሯል።
- ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የመጠጊያ፣ የመማጸኛ ከተማ የሚለው ቃል ሳያስበው ሰው የገደለ ሰው፣ የበቀል ጥቃት እንዳይደርስበት በፍጥነት በመሄድ የሚጠለልባቸውን ከተሞች ያመለክታል።
- ብዙውን ጊዜ ለሰዎች ወይም ለእንስሳት ከለላ የሚሆን ሕንፃ ወይም ጣራ፣ “መጠጊያ” ተብሎ ይጠራል።
- እንግዶቹ ከእርሱ ቤት ጣራ በታች “የተጠጉ” መሆናቸውን ሎጥ ከተናገረው መመልከት እንደሚቻለው፣ “መጠጊያ” – “መከለያ” ማለትም ይሆናል። ሎጥ እንዲህ ያለው በእርሱ ቤት እስካሉ ድረስ ምንም ጉዳት እንደማይደርስባቸው ለማመልከት ነው።