am_tw/bible/other/refuge.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መጠጊያ፥ መጠለያ
“መጠጊያ” የሚለው ቃል ዋስትናና ጥበቃ ያለበትን ቦታን ወይም ሁኔታን ያመለክታል። “መጠለያ” ከዝናብ ወይም ከአደጋ የሚከልል ነገር ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ሕዝቡ ጥበቃ፣ ጥንቃቄና ሰላም የሚያገኙበት መጠጊያ እንደ ሆነ ተነግሯል።
* ብሉይ ኪዳን ውስጥ፣ “የመጠጊያ፣ የመማጸኛ ከተማ የሚለው ቃል ሳያስበው ሰው የገደለ ሰው፣ የበቀል ጥቃት እንዳይደርስበት በፍጥነት በመሄድ የሚጠለልባቸውን ከተሞች ያመለክታል።
* ብዙውን ጊዜ ለሰዎች ወይም ለእንስሳት ከለላ የሚሆን ሕንፃ ወይም ጣራ፣ “መጠጊያ” ተብሎ ይጠራል።
* እንግዶቹ ከእርሱ ቤት ጣራ በታች “የተጠጉ” መሆናቸውን ሎጥ ከተናገረው መመልከት እንደሚቻለው፣ “መጠጊያ” “መከለያ” ማለትም ይሆናል። ሎጥ እንዲህ ያለው በእርሱ ቤት እስካሉ ድረስ ምንም ጉዳት እንደማይደርስባቸው ለማመልከት ነው።