am_tw/bible/other/push.md

819 B
Raw Permalink Blame History

መግፋት

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “መግፋት” ጉልበት በመጠቀም አንድን ነገር ማስወገድ ማለት ነው። የተለያዩ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።

  • “በኀይል መግፋት” ማለት፣ “መናቅ” ወይም፣ “ለመርዳት አለመፈለግ” ማለት ነው።
  • “ወደ ታች መግፋት” “መጨቆን” ወይም፣ “ማሳደድ” ወይም፣ “ማሸነፍ” ማለት ነው።
  • “አንድን ሰው ወደ ውጭ መግፋት” እርሱን ማራቅ ወይም ለዘለቄታው ማባረር ማለት ነው።
  • “ወደ ፊት መግፋት” ትክክል ወይም ተገቢ መሆኑን በቅጡ ሳይረዱ አንድን ነገር በማድረግ መቀጠል ማለት ነው።