# መግፋት ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “መግፋት” ጉልበት በመጠቀም አንድን ነገር ማስወገድ ማለት ነው። የተለያዩ ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት። * “በኀይል መግፋት” ማለት፣ “መናቅ” ወይም፣ “ለመርዳት አለመፈለግ” ማለት ነው። * “ወደ ታች መግፋት” – “መጨቆን” ወይም፣ “ማሳደድ” ወይም፣ “ማሸነፍ” ማለት ነው። * “አንድን ሰው ወደ ውጭ መግፋት” እርሱን ማራቅ ወይም ለዘለቄታው ማባረር ማለት ነው። * “ወደ ፊት መግፋት” ትክክል ወይም ተገቢ መሆኑን በቅጡ ሳይረዱ አንድን ነገር በማድረግ መቀጠል ማለት ነው።