am_tw/bible/other/purple.md

1.3 KiB

ሐምራዊ

“ሐምራዊ” የሰማያዊና የቀይ ቅልቅል የሆነ ቀለም ስም ነው። ልብስን በዚህ ቀለም ማቅለም በጣም ውድና ሰፊ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ ሐምራዊ ልብስ የሀብት፣ የከበሬታና የንጉሣዊነት ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ነበር።

  • በጥንት ዘመን ሐምራዊ በጥቂቱ የሚገኝና በጣም ውድ ልብስን ማቅለሚያ ቀለም ስለ ነበር የነገሥታትንና የሌሎች ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖችን ልብስ ለማቅለም ነበር ጥቅም ላይ የሚውለው።
  • ሐምራዊ ቀለም ከባሕር ቀንድ አውጣ ዐይነት ፍጡር ነበር የሚወጣው። ቀለሙን ለማውጣት ቀንድ አውጣውን መጨፍለቅ ወይም በሕይወት እያሉ እንዲለቁት በማድረግ ነበር። ይህ ደግም ጊዜና ጉልበት የሚጠይቅ ሂደት ነው።
  • እርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ በማለቱ ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት የሮም ወታደሮች ኢየሱስ ላይ ለማፌዝ ሐምራዊ ልብስ አልብሰውት ነበር።
  • የፊልጵስዩስ ነዋሪ የሆነችው ሊድያ ሐምራዊ ጨርቅ በመሸጥ የምትኖር ሴት ነበረች።