am_tw/bible/other/purple.md

9 lines
1.3 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ሐምራዊ
“ሐምራዊ” የሰማያዊና የቀይ ቅልቅል የሆነ ቀለም ስም ነው። ልብስን በዚህ ቀለም ማቅለም በጣም ውድና ሰፊ ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ ሐምራዊ ልብስ የሀብት፣ የከበሬታና የንጉሣዊነት ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ነበር።
* በጥንት ዘመን ሐምራዊ በጥቂቱ የሚገኝና በጣም ውድ ልብስን ማቅለሚያ ቀለም ስለ ነበር የነገሥታትንና የሌሎች ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖችን ልብስ ለማቅለም ነበር ጥቅም ላይ የሚውለው።
* ሐምራዊ ቀለም ከባሕር ቀንድ አውጣ ዐይነት ፍጡር ነበር የሚወጣው። ቀለሙን ለማውጣት ቀንድ አውጣውን መጨፍለቅ ወይም በሕይወት እያሉ እንዲለቁት በማድረግ ነበር። ይህ ደግም ጊዜና ጉልበት የሚጠይቅ ሂደት ነው።
* እርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነኝ በማለቱ ኢየሱስ ከመሰቀሉ በፊት የሮም ወታደሮች ኢየሱስ ላይ ለማፌዝ ሐምራዊ ልብስ አልብሰውት ነበር።
* የፊልጵስዩስ ነዋሪ የሆነችው ሊድያ ሐምራዊ ጨርቅ በመሸጥ የምትኖር ሴት ነበረች።