am_tw/bible/other/proclaim.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# ማወጅ፣ ዐዋጅ
አንድን ነገር በሕዝብ ፊት እና በድፍረት መናገር ወይም ማሳወቅ ማወጅ ይባላል።
* ብዙውን ጊዜ መጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ማወጅ” የሚለው እግዚአብሔር ያዘዘውን በግልጽ መናገርና እርሱ ምንኛ ታላቅ መሆኑን ለሌሎች መናገር ነው።
* ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ሐዋርያት በተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች ላሉ ብዙ ሰዎች የኢየሱስን የምሥራች ቃል ተናግረዋል።
* “ማወጅ” የሚለው ቃል ነገሥታት የሚያወጧቸውን ደንቦች ወይም ክፉ ነገርን በአደባባይ ማውገዝ ያመለክታል።
* “ማወጅ” የሚለውን ለመተርጎም፣ “ማሳወቅ” ወይም፣ “በግልጽ መስበክ” ወይ፣ “በአደባባይ መናገር” በተሰኙ ቃሎች መጠቀም ይቻላል።
* “ዐዋጅ” የሚለው ቃል፣ “ማስታወቂያ” ወይም፣ “ሕዝባዊ ስብከት” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።