am_tw/bible/other/prince.md

1.6 KiB

ልዑል፣ ልዕልት

“ልዑል” የሚባለው የንጉሥ ልጅ ነው። ሌሎችን መሪዎች ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል። “ልዕልት” የንጉሥ ልጅ ናት።

  • “ልዑል” የሚለው ብዙውን ጊዜ ገዢን፣ መሪን፣ ወይም ሥልጣን ያለውን ሌላ ሰው የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው።
  • አብርሃም ከነበረው ሀብትና ታላቅነት የተነሣ በመካከላቸው እየኖረ በነበረ ጊዜ ኬጢያውያን፣ “ልዑል” በማለት ጠርተውታል።
  • ኢየሱስም፣ “የሰላም ልዑል/አለቃ” እና፣ “የሕይወት ልዑል/አለቃ” ተብሏል።
  • ሐዋርያት ሥራ 2፡36 ላይ ኢየሱስ፣ “ጌታና ክርስቶስ” ተብሏል፤ ሐዋርያት ሥራ 5፡31 ላይ ደግሞ፣ “ልዑልና አዳኝ” ተብሏል፤ ይህም፣ “ጌታ” እና፣ “ልዑል” የሚለውን ተጓዳኝ ያሳያል።
  • ትንቢተ ዳንኤል ውስጥ፣ ስለ “ፋርስ አለቃ” እና፣ ስለ፣ “ግሪክ አለቃ” በተሰጠው ገለጻ ጥቅም ላይ የዋለው፣ “ልዑል” የሚለው ቃል ሲሆን፣ በእነዚህ አካባቢዎች ሥልጣን ወይም ኀይል የነበራቸውን ክፉ መናፍስት የሚያመለክት ሊሆንም ይችላል።
  • ትንቢተ ዳንኤል ውስጥ፣ የመላእክት አለቃ ሚካኤል፣ “ልዑል” ተብሏል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰይጣንም አልፎ አልፎ፣ “የዚህ ዓለም አለቃ/ልዑል” ተብሎአል።