am_tw/bible/other/precious.md

11 lines
1.1 KiB
Markdown

# ውድ፣ የተወደደ፣ ክቡር
“ውድ” የሚለው ቃል በጣም የተወደዱ፣ በጥቂቱ የሚገኙ ወይም ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸውን ሰዎች ወይም ነገሮችን ያመለክታል።
* “ክቡ ድንጋይ” ወይም፣ “የከበረ ዕንቁ” የተለያየ መልክ ያላቸውን ወይም ውብ የሚያደርጋቸው ባሕርያት ያላቸው ድንጋዮችና ማዕድኖችን ያመለክታል።
* ዕንቁ፣ አልማዝና ኤመራልድ የከበሩ ድንጋዮች ዐይነት ናቸው።
* ወርቅና ብርም፣ “የከበሩ ድንጋዮች” ይባላሉ።
* ሕዝቡ በእርሱ ፊት የከበሩ (ብርቅ) መሆናቸውን ያህዌ ይናገራል (ኢሳይያስ 43፡4)
* ገርና ጭምት መንፈስ በእግዚአብሔር ፊት ክብሩ ዋጋ እንዳለው ጴጥሮስ ጽፏል (1ጴጥሮስ 3፡4)።
* ይህ ቃል፣ “ክቡር” ወይም፣ “በጣም ውድ” ወይም፣ “ብርቅ” ወይም፣ “ከፍ ያለ ዋጋ (ግምት) ያለው” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።