980 B
980 B
ብሔር፣ ሕዝብ
“ብሔር” አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክተው ከአንድ ቅድመ አባት የተገኙትን ትውልዶችንና ተመሳሳይ ቋንቋና ባሕል ያላቸው ሰዎች ነው።
- የብሔር አባሎች አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ምድር ወይም አገር በአንድነት ይኖራሉ።
- የሕዝብ ስብስብ ከአንድ ወይም ከብዙ ነገዶች የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ።
- “ብሔር” አንዳንዴ፣ “ሕዝብ” ተብሎ ቢተረጎምም ሁለቱም ሁሌም አንድ ትርጕም የላቸው። “ብሔር” ግን የሚያመለክተው ሕዝብንና ባሕላቸውን ጭምር ነው።
- አንዳንዴ፣ “ሕዝብ” – “ብሔር” ለማለትም ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ፣ “ሕዝብህ” ሲባል፣ “ብሔርህ” ወይም፣ “ቤተ ሰብህ” ማለት ሊሆንም ይችላል።