# ብሔር፣ ሕዝብ “ብሔር” አብዛኛውን ጊዜ የሚያመለክተው ከአንድ ቅድመ አባት የተገኙትን ትውልዶችንና ተመሳሳይ ቋንቋና ባሕል ያላቸው ሰዎች ነው። * የብሔር አባሎች አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ምድር ወይም አገር በአንድነት ይኖራሉ። * የሕዝብ ስብስብ ከአንድ ወይም ከብዙ ነገዶች የተገኙ ሊሆኑ ይችላሉ። * “ብሔር” አንዳንዴ፣ “ሕዝብ” ተብሎ ቢተረጎምም ሁለቱም ሁሌም አንድ ትርጕም የላቸው። “ብሔር” ግን የሚያመለክተው ሕዝብንና ባሕላቸውን ጭምር ነው። * አንዳንዴ፣ “ሕዝብ” – “ብሔር” ለማለትም ጥቅም ላይ ይውላል። ለምሳሌ፣ “ሕዝብህ” ሲባል፣ “ብሔርህ” ወይም፣ “ቤተ ሰብህ” ማለት ሊሆንም ይችላል።