831 B
831 B
ታጋሽ፣ ትዕግሥት
“ታጋሽ” እና፣ “ትዕግሥት” የሚለው ቃል አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ መቋቋምን ወይም በዚያ ውስጥ በጽናት መኖርን ያመለክታል። አብዛኛውን ጊዜ ትዕግሥት መጠበቅንም ይጨምራል።
- አንድን ሰው መታገሥ ያ ሰው የቱንም ያህል በደል ቢፈጽም እርሱን መውደድና ይቅር ማለት ማለት ነው።
- ችግር ሲገጥማቸው የእግዚአብሔር ሕዝብ መታገሥና እርስ በርሳቸውም ትዕግሥተኞች መሆን እንደሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።
- ከምሕረቱ የተነሣ ቅጣት የሚገባቸው ኀጢአተኞች ቢሆኑም እግዚአብሔር ሕዝቡን ይታገሣል።