am_tw/bible/other/patient.md

8 lines
831 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ታጋሽ፣ ትዕግሥት
“ታጋሽ” እና፣ “ትዕግሥት” የሚለው ቃል አስቸጋሪ የሆነ ሁኔታ መቋቋምን ወይም በዚያ ውስጥ በጽናት መኖርን ያመለክታል። አብዛኛውን ጊዜ ትዕግሥት መጠበቅንም ይጨምራል።
* አንድን ሰው መታገሥ ያ ሰው የቱንም ያህል በደል ቢፈጽም እርሱን መውደድና ይቅር ማለት ማለት ነው።
* ችግር ሲገጥማቸው የእግዚአብሔር ሕዝብ መታገሥና እርስ በርሳቸውም ትዕግሥተኞች መሆን እንደሚገባቸው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል።
* ከምሕረቱ የተነሣ ቅጣት የሚገባቸው ኀጢአተኞች ቢሆኑም እግዚአብሔር ሕዝቡን ይታገሣል።