1.6 KiB
1.6 KiB
ማልቀስ፣ ለቅሶ
“ማልቀስ” እና፣ “ለቅሶ” የተሰኙት ቃሎች ጥልቅ የሐዘን መገለጫዎች ሲሆኑ፣ ብዙውን ጊዜ የሚያያዙት ሰው ሲሞት ከሚደረግ ሐዘን ጋር ነው። ብዙ ባሕሎች ሐዘንና ትካዜያቸውን የሚገልጡበት ውጫዊ እንቅስቃሴን ይጨምራል።
- እስራኤላውያንና በጥንት ዘመን የነበሩ ሌሎች ሕዝቦች ለቅሶዋቸውን የሚገልጡት ጮኽ ብሎ በሚሰማ ዋይታ ወይም እንጉርጉሮ ሲሆን፣ በአብዛኛው አሁን ያሉ ሕዝቦች ከሚያደርጉት ጋር ይመሳሰላል።
- ብዙውን ጊዜ ሰውየው ከሞተበት ጊዜ አንሥቶ መቃብር ውስጥ ከገባ ጥቂት ጊዜ በኋላ ድምፃቸውን አሰምተው ዋይ እንዲሉ አልቃሾች ይቀጠሩ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ አልቃሾች ሴቶች ነበሩ።
- መደበኛው የለቅሶ ጊዜ ሰባት ቀን ሲሆን፣ እስከ ሰለሣ ቀን (ሙሴና አሮን ሲሞቱ እንደ ተደረገው) ወይም እስከ ሰባ ቀን ድረስ (ያዕቆብ ሲሞት እንደ ተደረገው) ይቆይ ነበር።
- መጽሐፍ ቅዱስ በኀጢአት ምክንያት ስለ “ማልቀስ” ሲናገር ይህን ቃል በምሳሌነት ይጠቀማል። ኀጢአታችን ምን ያህል እግዚአብሔርን፣ ራሳችንንና ሌሎች ሰዎችን ምን ያህል እንደ ጎዳ በማሰብ ጥልቅ የሐዘን ስሜትንም ይጨምራል።