9 lines
1.6 KiB
Markdown
9 lines
1.6 KiB
Markdown
|
# ማልቀስ፣ ለቅሶ
|
||
|
|
||
|
“ማልቀስ” እና፣ “ለቅሶ” የተሰኙት ቃሎች ጥልቅ የሐዘን መገለጫዎች ሲሆኑ፣ ብዙውን ጊዜ የሚያያዙት ሰው ሲሞት ከሚደረግ ሐዘን ጋር ነው። ብዙ ባሕሎች ሐዘንና ትካዜያቸውን የሚገልጡበት ውጫዊ እንቅስቃሴን ይጨምራል።
|
||
|
|
||
|
* እስራኤላውያንና በጥንት ዘመን የነበሩ ሌሎች ሕዝቦች ለቅሶዋቸውን የሚገልጡት ጮኽ ብሎ በሚሰማ ዋይታ ወይም እንጉርጉሮ ሲሆን፣ በአብዛኛው አሁን ያሉ ሕዝቦች ከሚያደርጉት ጋር ይመሳሰላል።
|
||
|
* ብዙውን ጊዜ ሰውየው ከሞተበት ጊዜ አንሥቶ መቃብር ውስጥ ከገባ ጥቂት ጊዜ በኋላ ድምፃቸውን አሰምተው ዋይ እንዲሉ አልቃሾች ይቀጠሩ ነበር። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ አልቃሾች ሴቶች ነበሩ።
|
||
|
* መደበኛው የለቅሶ ጊዜ ሰባት ቀን ሲሆን፣ እስከ ሰለሣ ቀን (ሙሴና አሮን ሲሞቱ እንደ ተደረገው) ወይም እስከ ሰባ ቀን ድረስ (ያዕቆብ ሲሞት እንደ ተደረገው) ይቆይ ነበር።
|
||
|
* መጽሐፍ ቅዱስ በኀጢአት ምክንያት ስለ “ማልቀስ” ሲናገር ይህን ቃል በምሳሌነት ይጠቀማል። ኀጢአታችን ምን ያህል እግዚአብሔርን፣ ራሳችንንና ሌሎች ሰዎችን ምን ያህል እንደ ጎዳ በማሰብ ጥልቅ የሐዘን ስሜትንም ይጨምራል።
|