am_tw/bible/other/hard.md

8 lines
1.1 KiB
Markdown

# ጠንካራ፣ ጥንካሬ
“ጠንካራ” የሚለው ቃል እንደ ዐውዱ ሁኔታ የተለያዩ ትርጕሞች ይኖሩታል። ብዙዎን ጊዜ የሚያመለክተው አስቸጋሪ፣ አዳጋች ወይም የማይበገር ነገርን ነው።
* “ልበ ጠንካራ” የተሰኘው ፈሊጣዊ አነጋገር ግትርና ንስሐ የማይገቡ ሰዎችን ያመለክታል። ይህ አነጋገር ከክፉ ሥራቸው የተነሣ ከባድ መከራ ቢደርስባቸው እንኳ በእግዚአብሔር ላይ ማመፃቸውን የሚቀጥሉ ሰዎች መገለጫ ነው።
* “የልብ ጥንካሬ” እና “የልባቸው ጥንካሬ” የሚለው ምሳሌያዊ ገለጻም እንዲሁ ግትር አለመታዘዝን ያመለክታል።
* “ጠንክሮ መሥራት” ወይም፣ “ጠንክሮ መሞከር” ማለት በጽናትና በትጋት አንድን ነገር ማድረግ፣ አንድን ነገር ጥሩ አድርጎ ለመሥራት ከባድ ጥረት ማድረግን ያመለክታል።