1.8 KiB
1.8 KiB
እጅ፣ ቀኝ እጅ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “እጅ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር በበርካታ ቦታዎች ጥቅም ላይ ውሏል።
- ብዙውን ጊዜ “እጅ” የእግዚአብሔርን ኀይልና ሥራ ለማመልከት ተጠቅሷል፤ “እጁ ይህን ሁሉ አላደረገችምን?” እንደሚለው።
- “በእጅ ተላልፎ መሰጠት” የሚለው አገላለጽ አንድ ሰው በሌላው ሰው ቁጥጥር ሥልጣን ሥር እንዲሆን አሳልፎ መስጠትን ያመለክታል።
- “እጆችን መጫን” አንድን ሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት ለመለየት ወይም እንዲፈወስ ለመጸለይ እጆችን እርሱ ላይ ማድረግን ያመለክታል።
- “እጅ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውል፣ “እጆችህን አትጫን” ማለትም ማንንም አትጉዳ የሚለውን ይጨምራል።
- “ከ . . . እጅ ማዳን” አንድ ሰው ሌላውን እንዳይጎዳ ማስቆም ማለት ነው።
- “በቀኝ እጅ” በቀኝ በኩል ወይም በቀኝ ወገን ቦታ መያዝ ማለት ነው።
- በ . . . እጅ” የሚለው ሐረግ በዚያ ሰው እጆች የተከናወነ ወይም የተደረገ ተግባር ያመለክታል፤ ለምሳሌ፣ “በጌታ እጅ” ማለት ያንን ያደረገ እግዚአብሔር ነው ማለት ነው።
- ጳውሎስ፣ “ይህን በእጄ የጻፍኩ እኔ ነኝ” ሲል ያ መልእክት የተጻፈው እርሱ በቃል በሚነግረው በሌላው ሰው እጅ ሳይሆን በእርሱ ራሱ እጅ የተጻፈ መሆኑን ያመለክታል።