1.9 KiB
1.9 KiB
ፍየል
ፍየል መጠነኛ ቁመት ያለው፣ ከበግ ጋር የሚመሳሰልና በዋነኛነት ደረጃ ወተትና ሥጋ ለማግኘት ሰዎች የሚያረቡት ባለ አራት እግር እንስሳ ነው። የፍየል ግልገል “ወጠጤ” ይባላል።
- እንደ ብጎች ሁሉ ፍየሎችም መሥዋዕት ይቀርቡ ነበር፤ በተለይም ለመሥዋዕት የሚፍለጉት በፋሲካ በዓል ነበር።
- ምንም እንኳ ፍየሎች ከበጎች ጋር ቢመሳሰሉም በግልጽ የሚታዩ ጥቂት ልዩነቶችም አሏቸው።
- ፍየሎች ጥቁርና ሻካራ ጠጉር አላቸው፤ የበጎች ጠጉር ግን ሱፍ ልብስ ይሠራበታል።
- የፍየል ጭራ ወደ ላይ የቆመ ሲሆን የበግ ጭራ ግን የተንጠለጠለ ነው።
- ፍየሎች ጉጉ ስለሆኑ፣ ሌሎች ፍየሎች ባሉበት ቦታ አይሆኑም ወይም ሌሎች በሚሄዱበት አይሄዱም፤ በጎች ግን ከሌሎች በጎች ጋር አብረው መሆን ምቾት ይሰጣቸዋል፤ እረኛውን የመከተል ባሕርይም አላቸው።
- መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ፍየሎች በእስራኤል በዋናነት ደረጃ ወተት የሚገኘው ከፍየሎች ነበር።
- የፍየሎች ቆዳ ድንኳን የወይን ጠጅ የሚያዝበት ስልቻ መመሥሪያ ያገለግል ነበር።
- በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ፍየሎች የኀጢአተኞች ምሳሌ ተደርገው ይቀርቡ ነበር፤ ምናልባትም ለዚህ ምክንያቱ ፍየሎች ከሚጠቃቸው ሰው የመኮብለል ብርቱ ዝንባሌ ስላላቸው ሊሆን ይችላል።
- እስራኤላውያን ፍየሎችን እንደ የኀጢአት ተሸካሚ ምሳሌ ያደርጓቸው ነበር።