1.1 KiB
1.1 KiB
መታጠቂያ
“መታጠቂያ” የሚለው ቃል አንዳች ነገር ዙሪያ የሚታሰር ነገርን ነው። ብዙ ጊዜ የሚያመለክተው ቀሚስ ወይም እጀ ጠባብ ወደ መሬት እንዳይወርድ ወገብ ላይ ለማሰር የሚያገለግል ቀበቶ ወይም ሻሽን ነው።
- “ወገባችሁን ታጠቁ” የሚለው የተለመደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አነጋገር እግሮቻችሁ በፍጥነት መራመድ እንዲችሉ የልብሳችሁን ጫፍ ቀበቶአችሁ ውስጥ ሸጉጡት ማለት ነው።
- “መታጠቅ” በአንድ ነገር ዙሪያ መሄድ ማለትም ይሆልናል።
- ወገባችሁን ታጠቁ” የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጕሙ በሚሠራበት ቋንቋ ተመሳሳይ ትርጕም በሚሰጥ ፈሊጣዊ አነጋገር ሊተረጎም ይችላል። ወይም ደግም ምሳሌያዊ ባልሆነ አነጋገር፣ “ራሳችሁን ለተግባር አዘጋጁ” ወይም፣ “ተዘጋጁ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።