am_tw/bible/other/fruit.md

2.3 KiB

ፍሬ፣ ፍሬያማ

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ፍሬ” የሚበላ የተክል ክፍል ነው። “ፍሬያማ” ብዙ ፍሬ ያለው ማለት ነው። እነዚህ ቃሎች ምሳሌያዊ በሆነ ንግግር ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ።

  • መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሰውን ተግባርና ዐሳብ ለማመልከት፣ “ፍሬ” በሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ይጠቀማል። ዛፍ ላይ ያለው ፍሬ ዛፉ ምን ዓይነት መሆኑን እንደሚያሳይ ሁሉ፣ የአንድ ሰው ቃልና ተግባርም የእርሱን ማንነት ያሳያሉ።
  • አንድ ሰው መልካም ወይም መጥፎ መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራት ይችላል፤ ይሁን እንጂ፣ “ፍሬያማ” የሚለው ቃል ሁሌም የሚያመለክተው ብዙ መልካም ፍሬ መገኘቱን የሚያመለክተው አዎንታዊ ጎኑን ነው።
  • “ፍሬያማ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ፣ “ባለጸጋ” ማለትም ይሆናል። ይህም ባለ ብዙ ሀብት ወይም ምግብ እንደ መሆን ሁሉ. ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ያሉት መሆንን ይጨምራል።
  • አጠቃላይ በሆነ አነጋገር፣ “የ. . .ፍሬ” ከአንድ ሰው የሚመጣ ወይም ከእርሱ የሚገኝ ነገርን ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የጥበብ ፍሬ” ሲባል ጠቢብ በመሆን የተገኘ መልካም ነገርን ያመለክታል።
  • “የምድሪቱ ፍሬ” የሚለው ሐረግ ምድሪቱ የምታስገኘውን ሰዎች የሚመገቡትን በአጠቃላይ ያመለክታሉ። ይህም እንኳ እንደ ብርቱካን ወይም ማንጎ የመሳሰልቱን ፍሬዎች ብቻ ሳይሆን አትክልቶችን፣ ለውዝንና የእህል ዐይነቶችን ሁሉ ይጨምራል።
  • “የመንፈስ ፍሬ” የተሰኘው ምሳሌያዊ አነጋገር በሚታዘዙት ሰዎች ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚያስገኘው መንፈሳዊ ባሕርያት ያመለክታል።
  • “የማኅፀን ፍሬ” የሚለው ፈሊጣዊ ንግግር፣ “ከምኅፀን የሚገኘውን” ማለትም ልጆችን ያመለክታል።