# ፍሬ፣ ፍሬያማ ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ፍሬ” የሚበላ የተክል ክፍል ነው። “ፍሬያማ” ብዙ ፍሬ ያለው ማለት ነው። እነዚህ ቃሎች ምሳሌያዊ በሆነ ንግግር ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላሉ። * መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሰውን ተግባርና ዐሳብ ለማመልከት፣ “ፍሬ” በሚለው ቃል ብዙ ጊዜ ይጠቀማል። ዛፍ ላይ ያለው ፍሬ ዛፉ ምን ዓይነት መሆኑን እንደሚያሳይ ሁሉ፣ የአንድ ሰው ቃልና ተግባርም የእርሱን ማንነት ያሳያሉ። * አንድ ሰው መልካም ወይም መጥፎ መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራት ይችላል፤ ይሁን እንጂ፣ “ፍሬያማ” የሚለው ቃል ሁሌም የሚያመለክተው ብዙ መልካም ፍሬ መገኘቱን የሚያመለክተው አዎንታዊ ጎኑን ነው። * “ፍሬያማ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ መልኩ፣ “ባለጸጋ” ማለትም ይሆናል። ይህም ባለ ብዙ ሀብት ወይም ምግብ እንደ መሆን ሁሉ. ብዙ ልጆችና የልጅ ልጆች ያሉት መሆንን ይጨምራል። * አጠቃላይ በሆነ አነጋገር፣ “የ. . .ፍሬ” ከአንድ ሰው የሚመጣ ወይም ከእርሱ የሚገኝ ነገርን ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የጥበብ ፍሬ” ሲባል ጠቢብ በመሆን የተገኘ መልካም ነገርን ያመለክታል። * “የምድሪቱ ፍሬ” የሚለው ሐረግ ምድሪቱ የምታስገኘውን ሰዎች የሚመገቡትን በአጠቃላይ ያመለክታሉ። ይህም እንኳ እንደ ብርቱካን ወይም ማንጎ የመሳሰልቱን ፍሬዎች ብቻ ሳይሆን አትክልቶችን፣ ለውዝንና የእህል ዐይነቶችን ሁሉ ይጨምራል። * “የመንፈስ ፍሬ” የተሰኘው ምሳሌያዊ አነጋገር በሚታዘዙት ሰዎች ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ የሚያስገኘው መንፈሳዊ ባሕርያት ያመለክታል። * “የማኅፀን ፍሬ” የሚለው ፈሊጣዊ ንግግር፣ “ከምኅፀን የሚገኘውን” ማለትም ልጆችን ያመለክታል።