am_tw/bible/other/fountain.md

9 lines
994 B
Markdown

# ምንጭ
ምንጭ በተፈጥሮው ከመሬት የሚፈልቅ ወይም የሌላ ዓይነት ወራጅ ውሃ መነሻ ቦታ ነው።
* ይህ ቃል እግዚአብሔር የበረከት ምንጭ መሆኑን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።
* በዝመናችንም ለመጠጥ የሚሆን ውሃ የሚገኝባቸው ሰው ሠራሽ ጉድጓዶች ስላሉ በተፈጥሮ የተገኘውን ወራጅ ውሃ በሚያመለክት ቃል ወይም ሐረግ መጠቀሙ የተሻለ ይሆናል።
* ዘካርያስ 13፡1፣ “በዚያን ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል” ይላል።
* ማርቆስ 5፡29 ደም ደም ይፈስሳት ስለ ነበረችው ሴት ሲናገር፣ “የሚፈስሰው ደሟ (ምንጭ) ወዲያውኑ ቀመ” ይላል።