# ምንጭ ምንጭ በተፈጥሮው ከመሬት የሚፈልቅ ወይም የሌላ ዓይነት ወራጅ ውሃ መነሻ ቦታ ነው። * ይህ ቃል እግዚአብሔር የበረከት ምንጭ መሆኑን ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል። * በዝመናችንም ለመጠጥ የሚሆን ውሃ የሚገኝባቸው ሰው ሠራሽ ጉድጓዶች ስላሉ በተፈጥሮ የተገኘውን ወራጅ ውሃ በሚያመለክት ቃል ወይም ሐረግ መጠቀሙ የተሻለ ይሆናል። * ዘካርያስ 13፡1፣ “በዚያን ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል” ይላል። * ማርቆስ 5፡29 ደም ደም ይፈስሳት ስለ ነበረችው ሴት ሲናገር፣ “የሚፈስሰው ደሟ (ምንጭ) ወዲያውኑ ቀመ” ይላል።