am_tw/bible/other/fast.md

9 lines
874 B
Markdown

# ጾም
መጾም ምግብን ወይም አንዳንድ የምግብ ዐይነቶችንና መጠጦችን ለተወሰነ ጊዜ ማቆም ነው።
* ጾም ሰዎች ትኩረታቸውን እግዚአብሔር ላይ እንዲያደርጉና በምግብ አስተሳሰባቸው ሳይበታተን መጸለይ እንዲችሉ ይረዳል።
* የተሳሳተ ዓላማ ይዞ በመጾም ኢየሱስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎችን ተቃውሞ ነበር። ይጾሙ የነበረው ምን ያህል ሃይማኖተኞች መሆናቸውን ሌሎች እንዲያዩላቸው ነበር።
* አንዳንዴ ሰዎች የሚጾሙት በአንድ ነገር ምክንያት በጣም ማዘናቸውንና መተከዛቸውን ለማሳየት ነው።
* ይህ ቃል፣ “መመገብን መተው” ተብሎ መተርጎም ይችላል።