# ጾም መጾም ምግብን ወይም አንዳንድ የምግብ ዐይነቶችንና መጠጦችን ለተወሰነ ጊዜ ማቆም ነው። * ጾም ሰዎች ትኩረታቸውን እግዚአብሔር ላይ እንዲያደርጉና በምግብ አስተሳሰባቸው ሳይበታተን መጸለይ እንዲችሉ ይረዳል። * የተሳሳተ ዓላማ ይዞ በመጾም ኢየሱስ የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎችን ተቃውሞ ነበር። ይጾሙ የነበረው ምን ያህል ሃይማኖተኞች መሆናቸውን ሌሎች እንዲያዩላቸው ነበር። * አንዳንዴ ሰዎች የሚጾሙት በአንድ ነገር ምክንያት በጣም ማዘናቸውንና መተከዛቸውን ለማሳየት ነው። * ይህ ቃል፣ “መመገብን መተው” ተብሎ መተርጎም ይችላል።