am_tw/bible/other/dove.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# ርግብ፣ ዋኖስ
ርግብና ዋኖስ በጣም የሚመሳሰሉ የተለያየ መልክ ያላቸው ትናንሽ ወፎች ናቸው። ርግብ በምጠኑ ፈካ ያለች ስትሆን ወደ ነጭነት ትጠጋለች።
* በአንድ ቋንቋዎች ሁለት የተለያዩ ስሞች ሲኖሯቸው፣ ሌሎች ግን ሁለቱንም በአንድ ስም ይጠሯቸዋል።
* ርግብና ዋኖስ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይቀርቡ ነበር፤ በተለይም ትልቅ እንስሳ መሥዋዕት ለማቅረብ ዐቅማቸው የማይፈቅድ ሰዎች እነዚህን ወፎች ነበር የሚያቀርቡት።
* ርግብ ጎርፍ ሲጎድል የወይራ ቅጠል ይዛ ወደ ኖኅ መጣች።
* ርግቦች ንጽሕናን፣ ጨዋነትንና ሰላምን ይወክላሉ።
* ትርጕም በሚሠራበት ቋንቋ ርግብና ዋኖስ የማይታወቁ ከሆነ፣ “ርግብ ተብሎ የምትጠራ ትንሽ ወፍ” ወይም፣ “. . . የምትመስል (ያገሩን ወፍ) ትንሽ ወፍ” ብሎ መተርጎም ይቻላል።