am_tw/bible/other/destroyer.md

8 lines
897 B
Markdown

# አጥፊ
ቃል በቃል ሲወስድ፣ “አጥፊ” የሚለው ቃል፣ “የሚያጠፋ ሰው” ማለት ነው።
* ይህ ቃል ብሉይ ኪዳን ውስጥ ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ የዋለው ወራሪ ሠራዊት እንደሚያደርገው ሌላውን ሕዝብ የሚያጠፋ ለማለት ነው።
* የግብፃውያንን በኩር ወንዶች እንዲገድል እግዚአብሔር የላከው መልአክ፣ “የበኩር ልጆችን የሚያጠፋ” ተብሎ ተጠርቷል።
* ከዮሐንስ ራእይ እንደምንመለከተው በመጨረሻው ዘመን ሰይጣን ወይም ርኩሳን መናፍስት፣ “አጥፊ” ተብለዋል። “አጥፊው” እርሱ ራሱ ነው፤ ምክንያቱም የእርሱ ዓላማ እግዚአብሔር የፈጠረውን ሁሉ ማጥፋትና ማበላሸት ነው።