am_tw/bible/other/desecrate.md

9 lines
1021 B
Markdown

# ማርከስ፣ ማጉደፍ
ለአምልኮ ጥቅም ላይ ማዋል በማይቻልበት ሁኔታ የተቀደሰ ቦታን ወይም ነገርን መጉዳት ወይም መበከል ማለት ነው።
* ለአንድ ነገር አክብሮትን አለማሳየት ብዙውን ጊዜ ያንን ነገር ማርከስ ወይም ማጉደፍ ማለት ነው።
* ለምሳሌ ቤተ መንግሥታቸው ውስጥ ለግብዣ በመጠቀም አረማውያን ነገሥታት ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተወሰዱ የተለየ ክብር ያላቸው ዕቃዎችን አርክሰዋል ወይም አጉድፈዋል።
* በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የነበረውን መሠዊያ ለማርከስ ወይም ለማጉደፍ ጠላቶች የሞተ ሰው አጥንት ተጠቅመው ነበር።
* ይህ ቃል፣ “ቅድስና መንፈግ” ወይም፣ “ክብር መንፈግ” ወይም “ማቆሸሽ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።