am_tw/bible/other/decree.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# ዐዋጅ
ዐዋጅ የሚባለው ሕግን ወይም መምሪያን ለሰዎች በአደባባይ በግልጽ መናገር ነው።
* የእግዚአብሔር ሕጎችም ዐዋጅ፣ መመሪያ ወይም ትእዛዞች ተብለዋል።
* እንደ ሕግና ትእዛዝ ሁሉ ሰዎች ለዐዋጅም መታዘዝ አለባቸው።
* አንድ ሰብዓዊ መሪ ላደረገው ዐዋጅ ምሳሌ የሚሆነን በሮም የሚኖር ሰው ሁሉ ወደ ተወለደበት አካባቢ ሄዶ እንዲቆጠር ያዘዘው የአውጉስጦስ ቄሳር ዐዋጅ ነው።
* አንድ ነገር ማወጅ ልንታዘዘው የሚገባ ትእዛዝ መስጠት ማለት ነው። ይህም፣ “ማዘዝ” ወይም፣ “መናገር” ወይም፣ “መመሪያ መስጠት” ተብሎ መተርጎም ይችላል።
* “ዐዋጅ” ተነገረ ማለት ያ ነገር፣ “በእርግጥ ይሆናል” ወይም፣ “ያ ነገር በፍጹም አይለወጥም” ወይም፣ “ያ ነገር እንዲደረግ ተወስኖአል” ማለት ነው።