1.1 KiB
1.1 KiB
ጨለማ
ቃል በቃል፣ “ጨለማ” የብርሃን አለመኖር ማለት ነው። ይህ ቃል የተለያዩ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።
- እንደ ተዋጭ ዘይቤ፣ “ጨለማ” – “ርኵሰት” ወይም፣ “ክፉ” ወይም፣ “መንፈሳዊ ዕውርነት” ማለት ነው።
- ማንኛውም ኀጢአትና ግብረ ገባዊ ብልሽትንም ሊያመለክት ይችላል።
- “የጨለማ ግዛት” የሚለው አገላለጽ ክፉ የሆነውንና በሰይጣን የተገዛውን ሁሉ ያመለክታል።
- “ጨለማ” የሞት ተለዋጭ ዘይቤ በምሆንም ያገለግላል።
- እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች፣ “ጨለማ ውስጥ እየኖሩ ነው” ይባላል፤ ይህም የጽድቅ አኗኗርን መረዳት አይችሉም ማለት ነው።
- እግዚአብሔር ብርሃን ነው (ጽድቅ) ጨለማም (ክፉ) በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።
- እግዚአብሔርን የሚንቁ ሰዎች የሚቀጡበት ቦታ አንዳንድ፣ “በውጭ ያለው ጨለማ” ይባላል።