am_tw/bible/other/darkness.md

12 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጨለማ
ቃል በቃል፣ “ጨለማ” የብርሃን አለመኖር ማለት ነው። ይህ ቃል የተለያዩ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።
* እንደ ተዋጭ ዘይቤ፣ “ጨለማ” “ርኵሰት” ወይም፣ “ክፉ” ወይም፣ “መንፈሳዊ ዕውርነት” ማለት ነው።
* ማንኛውም ኀጢአትና ግብረ ገባዊ ብልሽትንም ሊያመለክት ይችላል።
* “የጨለማ ግዛት” የሚለው አገላለጽ ክፉ የሆነውንና በሰይጣን የተገዛውን ሁሉ ያመለክታል።
* “ጨለማ” የሞት ተለዋጭ ዘይቤ በምሆንም ያገለግላል።
* እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች፣ “ጨለማ ውስጥ እየኖሩ ነው” ይባላል፤ ይህም የጽድቅ አኗኗርን መረዳት አይችሉም ማለት ነው።
* እግዚአብሔር ብርሃን ነው (ጽድቅ) ጨለማም (ክፉ) በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።
* እግዚአብሔርን የሚንቁ ሰዎች የሚቀጡበት ቦታ አንዳንድ፣ “በውጭ ያለው ጨለማ” ይባላል።