am_tw/bible/other/cupbearer.md

9 lines
937 B
Markdown

# ወይን ጠጅ ኀላፊ
በብሉይ ኪዳን ዘመን፣ “ወይን ጠጅ ኀላፊ” ለንጉሡ ወይን በጽዋ የሚያቀርብ ሰው ሲሆን፣ ወይኑ ያልተመረዘ መሆኑን ለማረጋገጥ ብዙውን ጊዜ ኀላፊው መጀመሪያ እንዲቀምስ ይደረግ ነበር።
* ቃል በቃል ትርጕሙ፣ “ጽዋ አቅራቢ” ወይም፣ “ጽዋውን የሚያቀርብ ሰው” ማለት ነው።
* ወይን ጠጅ ኀላፊ በንጉሡ ዘንድ የተወደደና እምነት የሚጣልበት ነበር።
* ታማኝና ከመሆኑ የተነሣ ወይን ጠጅ ኀላፊው መሪው በሚያደርገው ውሳኔ ተጽዕኖ የማሳደር ዐቅም ነበረው።
* ነህምያ እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮ ውስጥ በነበሩ ዘመን የፋርስ ንጉሥ የአርጤክስስ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበር።