ገለባ
ደረቅ የእህል ዘር መከላከያ ሽፋን ነው። ገለባ ለምግብነት አይጠቅምም፤ ስለዚህም ከእህሉ እንዲለያይ ይደረግና በኋላ ይጣላል።
- ብዙውን ጊዜ ገለባው ከእህሉ የሚለየው እህሉን ወደ አየር በመበተን ነበር፤ ነፋስ ገለባውን ይወስደዋል፣ እህሉ ግን መሬት ላይ ይወድቃል። ይህ ሂደት “ማበራየት” ይባላል።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል ክፉ ሰዎችንና ጥቅም የሌለው ነገርን ለማመልከት በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል።