am_tw/bible/other/caughtup.md

8 lines
968 B
Markdown

# መንጠቅ፣ ነጠቀ
ብዙውን ጊዜ፣ “መንጠቅ” የሚለው ቃል ተአምራዊ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር በድንገት አንድን ሰው ወደ ሰማይ ሲወስድ ነው።
* “ነጠቀ” የሚለው ቃል በፍጥነት አንድ ሰው ላይ መድረስ ማለት ነው። ከዚህ ቃል ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ያለው፣ “አስገድዶ መያዝ” የሚለው ነው።
* ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ እርሱን በአየር ለመቀበል ክርስቲያኖች በአንድነት እንደሚነጠቁ ጳውሎስ ይናገራል።
* “ኃጢአቴ ያዘኝ” የተሰኘው ምሳሌያዊ አንጋገር፣ “የኃጢአቴን ውጤት እየተቀበልሁ ነው” ወይም፣ “ከኃጢአቴ የተነሣ እየተሰቃየሁ ነው” ወይም፣ “ኃጢአቴ ችግር አምጥቶብኛል” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።