am_tw/bible/other/burden.md

1.3 KiB

ሸክም

ሸክም ከባድ ጫና ነው። ቃል በቃል የጥንት እንስሳት የሚሸከሙትን ሸክም ያመልክታል። “ሸክም” የሚለው ቃል በርካታ ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሉት።

  • ሸምክ አንድ ሰው መፈጸም ያለበትን ከባድ ሥራን ወይም ጠቃሚ ኀላፊነትንም ማመልከት ይችላል። ከባድ ሸክም፣ “ተሸክሞአል” ወይም፣ “ከባድ ጫና ተጭኖታል” ማለት ይቻላል።
  • አንድ ጨካኝ መሪ ሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም ሊጭን ይችላል፤ ለምሳሌ ብዙ ግብር ወይም ቀረጥ እንዲከፍሉ በማስገደድ።
  • ሌላው ላይ ሸክም መሆን የማይፈልግ ሰው እዚያ ሰው ላይ ችግር መፍጠር አይፈልግም።
  • ኃጢአት የሚያስከትለው በደለኝነት ለዚያ ሰው ሸክም ነው።
  • “የጌታ ሸክም” የሚለው ምሳሌያዊ አገላለጽ አንድ ነቢይ ለእግዚአብሔር ሕዝብ ያለበትን፣ “የእግዚአብሔር ሸክም” ያመለክታል።
  • “ሸክም” የተሰኘው ቃል፣ በምንባቡ ዐውድ መሠረት፣ “ኃላፊነት” ወይም፣ “ተግባር” ወይም፣ “መልእክት” ተብሎ ሊተርጎም ይችላል።